Notice

የካቲት 01 ቀን 2016 ዓ.ም

ማስታወቂያ

በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና የትምህርት አመራሮች ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ በ2016 በጀት አመት የሁለተኛ ደረጃ መምህራንን አቅም ለማጎልበት የሚያግዝ ልዩ የስልጠና መረሃግብር ለማዘጋጀት እየሰራ ይገኛል።

በዚሁ መሰረት ስልጠናው የመምህራንን የስልጠና ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ እንዲሆን ለማድረግ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ከሚገኙ መምህራን መርጃ ለመሰብስብ የሚያስችል የበይነ መረብ መጠይቅ ተዘጋጅቷል።

በመሆኑም በማንኛውም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሒሳብ፣ እንግሊዘኛና የተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዓይነቶችን የምታስተምሩ መምህራን

 https://forms.office.com/r/B8GAUYUg4H

ላይ በመግባት የተዘጋጀውን መጠይቅ እንድትሞሉና ለሚዘጋጀው ስልጠና ጥራት አስተዋፅኦ እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

የትምህርት ሚኒስቴር!


ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም

ማስታወቂያ

ለድጋሚ (Re-exam) ተፈታኞች በሙሉ

የካቲት 6/2016 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለመፈተን በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ የድጋሚ (Re-exam) ተፈታኞች በሙሉ የመፈታኛ የይለፍቃል (Password) ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

  1. በምዝገባ ወቅት በሞላችሁት email በኩል
  2. https://exam.ethernet.edu.et ላይ በመግባት የከፈላችሁበትን Transaction Number በማስገባት እንዲሁም
  3. ከተመደባብችሁብት የመፈተኛ ተቋም ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ

  • ለመጀመሪያ ጊዜ የመዉጫ ፈተና የምትፈተኑ እጩ ተመራቂዎች የይለፍቃል (Password) የምታገኙት ከምትማሩበት ወይም ከተመደባብችሁበት የመፈተኛ ተቋም ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን።
  • ሁሉም ተፈታኞች የሞዴል ፈተናን እስከ  የካቲት 5/2016 ዓ.ም መውሰድ ይኖርባቸዋል።

ትምህርት ሚኒሰቴር !


ጥር 27 ቀን 2016 ዓ.ም

የቀን ለውጥ ማስታወቂያ

ረቂቅ መመሪያዎች ላይ አስተያየት ለመስጠት ሀሙስ የተጠራው ስብሰባ ወደ አርብ የካቲት 1/2016 ዓ.ም ጠዋት 3:30  ሰዓት መሸጋገሩን ስለማሳወቅ

የትምህርት ሚኒስቴር: –

  1. የአጠቃላይ ትምህርት የመምህራን የደረጃ እድገት የአፈጻጸም መመሪያ፣
  2. የር/መምህራን፣ የም/ር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የምልመላ መረጣና ምደባ የአፈጻጸም መመሪያ፣
  3. የቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ዕጩ መምህራን ምልመላና መረጣ የአፈጻጸም መመሪያ፣ የሚሉ 3 መመሪያዎችን አዘጋጅቷል።

መመሪያዎቹ በተለያየ ጊዜ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት አስተያየት ሰጥተውባቸው የዳበሩ ሲሆን የፌደራል አስተዳደር ስነ-ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 ክፍል 2 ንዑስ ክፍል 2 አንቀጽ 10 መሰረት የሚዘጋጁ መመሪያዎች ከመጽደቃቸው በፊት ማንኛውም ሰው የሚሳተፍበት የውይይት መድረክ ማዘጋጀትና ግብዓት መሰብሰብ እንዳለበት ስለሚደነግግ ሚኒስቴሩ የውይይት መድረከ አዘጋጀቷል።

በዚህም መሰረት አርብ የካቲት 01/2016 ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ በትምህርት ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ለባለድርሻ አካላት የገለጻና የውይይት መድረክ ስለተዘጋጀ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ በመገኘት አስተያየት እንድትሰጡ ተጋብዛችኋል።


ጥር 24 ቀን 2016 ዓ.ም

ማስታወቂያ

ረቂቅ መመሪያዎች ላይ አስተያየት እንድትሰጡ ስለመጋበዝ

የትምህርት ሚኒስቴር: –
1. የአጠቃላይ ትምህርት የመምህራን የደረጃ እድገት የአፈጻጸም መመሪያ፣
2. የር/መምህራን፣ የም/ር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የምልመላ መረጣና ምደባ የአፈጻጸም መመሪያ፣
3. የቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ዕጩ ምምህራን ምልመላና መረጣ የአፈጻጸም መመሪያ፣ የሚሉ 3 መመሪያዎችን አዘጋጅቷል።
መመሪያዎቹ በተለያየ ጊዜ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት አስተያየት ሰጥተውባቸው የዳበሩ ሲሆን የፌደራል አስተዳደር ስነ-ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 ክፍል 2 ንዑስ ክፍል 2 አንቀጽ 10 መሰረት የሚዘጋጁ መመሪያዎች ከመጽደቃቸው በፊት ማንኛውም ሰው የሚሳተፍበት የውይይት መድረክ ማዘጋጀትና ግብዓት መሰብሰብ እንዳለበት ስለሚደነግግ ሚኒስቴሩ የውይይት መድረከ አዘጋጀቷል።
በዚህም መሰረት ጥር 30/2016 ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ በትምህርት ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ለባለድርሻ አካላት የገለጻና የውይይት መድረክ ስለተዘጋጀ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ በመገኘት አስተያየት እንድትሰጡ ተጋብዛችኋል።


21/05/2016

ስ ታ ወ ቂ ያ

የመውጫ ፈተና መመዝገቢያ ጊዜ እስከ 20/2016ዓ.ም መራዘሙን ስለማሳወቅ

በ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለመፈተን የምዝገባ ጊዜው ጥር 08/2016 ዓ.ም ጀምሮ ጥር 15/2016 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ መጠቀሱ የሚታወሰ ነው።

ይሁን እንጂ በተፈታኞች ጥያቄ መሰረት የምዝገባ ጊዜው እስከ ጥር 20/2016 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን እያሳወቅን ሌሎች ሁኔታዎች ግን ቀደም ሲል በተገለጸው አግባብ የሚከናወኑ መሆኑን እናሳውቃለን።

=========================

የመውጫ ፈተና በድጋሚ ለምትፈተኑ አመልካቾች በሙሉ

ከ2015 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም በቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች ለእጩ ተመራቂ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ላይ የመውጫ ፈተናን ለመፈተን በመጠባበቅ ላይ ያላችሁ ተፈታኞች በሙሉ ፈተናው ከጥር 27- የካቲት 1/2016 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ስለሆነም በሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተናውን ተፈትናችሁ ያላለፋችሁ እና ከጥር 27 – የካቲት 1/ 2016 ዓ.ም ድረስ የመውጫ ፈተናውን በድጋሚ (Re-exam) ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ያላችሁ ተፈታኞች በሙሉ ምዝገባ የምታካሂዱትና የመፈተኛ ተቋም (የመንግስት ዩኒቨርሲቲ) የምትመርጡት ከታች በተገለጸው ማስፈንጠሪያ (Link)

(https://exam.ethernet.edu.et)

ስለሆነ፣ ከጥር 08 እስከ ጥር 20 2016 ዓ.ም ድረስ የምዝገባ ክፍያ 500.00 ብር በቴሌ ብር ብቻ በመክፈል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

አመልካቾች ተጨማሪ ድጋፍ የምትፈልጉ ከሆነ በስልክ ቁጥር +251 118 13 21 76 ወይም በኢሜይል registration@ethernet.edu.et በኩል ድጋፍ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ማሳሰቢያ

ለመጀመሪያ ጊዜ የመዉጫ ፈተና የምትፈተኑ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ የምታካሂዱት እና የአገልግሎት ክፍያ የምትፈፅሙት በተቋማችሁ በኩል መሆኑን እየገለጽን አስፈላጊው የመፈተኛ መረጃዎች በተቋማችሁ የሚደርሳችሁ መሆኑን እናሳውቃል።


19/04/16

በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪ ጥሪና ትምህርት ማስጀመርን አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

.በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከጥር 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሁለት ሳምንታት ትምህርት ይጀምራሉ፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ክልል በተፈጠረው ወቅታዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች በ2016 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያዉ ወሰነ-ትምህርት ተማሪዎቻቸውን ለመጥራትና መደበኛ የመማር ማስተማር ስራቸዉን ሙሉ ለሙሉ ለመጀመር አልቻሉም ነበር።

በመሆኑም የትምህርት ሚኒስቴር ከክልሉ ኮማንድፖስት፣ የጸጥታ አደረጃጀቶችና የሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ተከታታይ ውይይቶችን ሲያካሂድ ቆይቷል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ፣ የአስሩ ዩኒቨርስቲዎች ፕሬዝዳንቶችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የክልሉ ጸጥታ አካላት ትናንት ታህሳስ 18/2016 ዓ.ም በጉዳዩ ዙሪያ የመከሩ ሲሆን አሁን በክልሉ አንጻራዊ ሰላም የተፈጠረ በመሆኑ ዩኒቨርስቲዎቹ ተማሪዎችን መጥራትና ማስተማር እንደሚችሉ ውሳኔ ላይ ተደርሷል።

በዚህም መሰረት ከጥር 1/2016 ጀምሮ ባሉ ሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ዩኒቨርስቲዎቹ ተማሪዎችን ጠርተው የመማር ማስተማር ስራቸውን ይጀምራሉ።

በመሆኑም በአማራ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የተመደባችሁ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲዎቹ የሚያደርጉትን ጥሪ እንድትከታተሉ እንገልጻለን።በ 2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ)  ለመማር ያለፋችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን በየትምህርትቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ ጥቅምት 14/2016 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ፡   በልዩ ሁኔታ በአዳማ እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲዎች መማር የምትፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ ምርጫችሁ ውስጥ በማካተት መመደብ የምትችሉ መሆኑ እናሳውቃለን።

የትምህርት ሚኒስቴር