ማስታወቂያ
በ2017 ዓ.ም በሰኔ ወር የሚሰጠው የመውጫ ፈተና መመዝገቢያ ጊዜ እስከ ግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ብቻ የተራዘመ መሆኑን እየገለጽን፡-
1. እስከ አሁን ያልተመዘገባችሁ የድጋሚ ተፈታኞች (resitters) ከዚህን በፊት ለምዝገባ በተከፈተውና በተገለጸው መመዝገቢያ ፕላትፎረም (registration link) በኩል ገብታችሁ ምዝገባችሁን እንድታጠናቅቁ፣
2. ለመጀመሪያ ጊዜ ለመውጫ ፈተና የምትቀመጡ ተፈታኞች በተቋሞቻችሁ በኩል መመዝገባችሁን እንድታረጋግጡ እያሳሰብን፤
3. ፈተናው የሚሰጠው ከሰኔ 2-10/2017 ዓ.ም መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ማሳሰቢያ
ለፈተናው የምታመለክቱ አመልካቾች ለመመዝገብ የብሔራዊ መታወቂያ ካርድ ሊኖራችሁ ይገባል፡፡
ከግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ቦኋላ ምዝገባ አይስተናገድም፡፡
የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር