የፋርማሲ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናን (Exit Exam) አስመልክቶ የተዘጋጀ ተጨማሪ ማብራሪያ
የ2016 ዓ.ም የፋርማሲ ትምህርት ክፍል እጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) በድጋሚ ቅዳሜ ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በጠዋትና በከሰዓት በሁለት ፈረቃ እንደሚሰጥ ማሳወቃችን ይታወቃል።
ሆኖም ከተፈታኞች ቁጥር አንጻር ፈተናው በተጠቀሰው ቀን ጠዋት ከ2:30 ሰዓት ጀምሮ ለግማሽ ቀን ብቻ የሚሰጥ መሆኑን እያሳወቅን ከዚህ የሚከተለው ተጨማሪ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
- በዚህ ፈተና የሚቀመጡት ለመጀመሪያ ጊዜ የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተፈታኞች (First seater) እና ፣
- ከዚህ በፊት የመውጫ ፈተና ተፈትነዉ የማለፊያ ውጤት ያላገኙ ተፈታኞች (re-takers) ናቸው።
ትምህርት ሚኒስቴር ይህንን የመውጫ ፈተና በዩኒቨርስቲዎች ትምህርታቸውን ተከታትለው ላጠናቀቁ ተማሪዎች መውጫ ያዘጋጀው መሆኑ ታውቆ የፋርማሲ ትምህርት ክፍል እጩ ተመራቂዎች በጤና ሚኒስቴር የሚዘጋጀውን የላይሰንሰር ፈተና በሌላ ጊዜ እንደሚሰጣችሁ እንድትገነዘቡ እያሳወቅን ጊዜው ወደፊት በሚወጣ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል።