ማስታወቂያ
ለፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን አወዳድረን ለመቅጠር የምዝገባ ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወቃል።
ነገር ግን የዘንድሮ የክረምት ልዩ የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች አቅም ግንባታ ስልጠና የተጠናቀቀው በቅርቡ በመሆኑ ምዝገባውን ማራዘም አስፈልጓል። በመሆኑም ምዝገባው እስከ ጳጉሜን 05/2017 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ መሆኑንን እየገለጽን ለማመልከት ፍላጎቱ ያላችሁ መምህራን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ እድትመዘገቡ በድጋሚ እንገልጻለን ። ለመመዝገብ https://sbs.moe.gov.et/career/teacher ይጠቀሙ
