ማስታወቂያ
ለወሊሶ ፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነባርና አዲስ ተማሪዎች በሙሉ፦
በወሊሶ ፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስትማሩ ለነበራችሁ ነባር ተማሪዎች እንዲሁም በ2019 ዓ.ም በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤቱ የመግቢያ ቀናት ህዳር 1 እና 2/2019 ዓ.ም መሆኑን እንገልጻለን።
በተጨማሪም፣ ህዳር 3 ቀን 2019 ዓ.ም ለተማሪዎች የኦረንቴሽን መርሃ ግብር የሚካሄድ ሲሆን፣ ህዳር 4 ቀን 2019 ዓ.ም ደግሞ የመማሪያ መጻሕፍት ስርጭት ይከናወናል።
ስለሆነም ሁላችሁም ነባርና አዲስ ተመዳቢ ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት በወሊሶ ፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ምዝገባችሁን እንድታከናውኑ እናሳስባለን።
መልካም የትምህርት ዘመን!
የትምህርት ሚኒስቴር
ለወሊሶ ፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነባርና አዲስ ተማሪዎች በሙሉ
