ማስታወቂያ
በ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ላመጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤
በ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ለመማር ፍላጎት ያላችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 14/2018 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ማሳሰቢያ፡-
1. የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ተማሪዎችን ስሚቀበል ምርጫችሁ ውስጥ ማካተት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
2. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እና አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ምርጫ ውስጥ የማይካተቱ መሆኑ እናሳውቃለን።