ከሰኔ 14 እስከ 19 ቀን 2016 ዓ. ም በ 244 ፕሮግራሞች በ57 የመንግስትና በ124 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለነበሩ ተማሪዎች የመዉጫ ፈተና ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ለስድስት ቀናት ያለምንም እንከን የተሰጠው ፈተና ያለምንም እንከን የተጠናቀቀ ሲሆን ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የተሰጠዉ የፋርማሲ ፈተና ብቻ የቴክኒክ ችግር አጋጥሞታል። ስለሆነው ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎቹ ፈተናውን በድጋሜ እንዲወስዱ አመቻችቷል።
በዚሁ መሰረት ፈተናው በድጋሜ ቅዳሜ ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጠዋት ከ 3:00 ሰአት ጀምሮ እና ከሰአት ከ 8:00 ሰአት ጀምሮ ስለሚሰጥ ለፈተናው ተቀምጣችሁ የነበራችሁ የፋርማሲ ተማሪዎች በተፈተናችሁበት የፈተና ጣቢያ በሰዓቱ በመገኘት በድጋሜ የሚሰጠውን ፈተና እንድትወስዱ እናሳስባለን፡፡