በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ውሳኔን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ
መስከረም /2017
ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡትን አነስተኛ የተማሪዎች ቁጥር ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ውጤት መቀነስ በትምህርት ዘርፉ እና በአጠቃላይ በሀገር ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ማህበራዊ፣ ስነ ልቦናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እንዲሁም ተዛማጅ ችግሮችን ከግምት ውስጥ በማስገባት የገጠመውን የውጤት መቀነስ ለማስተካከል የማካካሻ ትምህርት (Remedial Program) በተመረጡ የትምህርት አይነቶችና ይዘቶቻቸው ላይ በማስተማር እና የመመዘኛ ፈተና በመስጠት ምዘናውን የሚያልፉ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በመደበኛ ፕሮግራም እንዲቀጥሉ መወሰኑ ይታወቃል።
በመሆኑም የ2017 የትምህርት ዘመን የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን በተፈጥሮ ሳይንስና ማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ያላቸዉን የቅበላ አቅምን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial Program) የመግቢያ ነጥብ መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ ፈተናዉን የወሰዱና ከ50 ከመቶ በታች ያስመዘገቡ ነገር ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የ Remedial ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ይሆናሉ ።
- በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 31% ከመቶ እና ከዚያ የተቆረጠ መሆኑን።
- ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ ይሆናሉ።
ተ.ቁ | መግለጫ | ጠቅላላ ውጤት | የመግቢያ ውጤት |
1 | የተየፈጥሮ እና የማሀበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች | 600 | 204 |
2 | የተየፈጥሮ እና የማሀበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች | 600 | 192 |
3 | ታዳጊ ክልልና አርብቶ አደር አካባቢ የተየፈጥሮና ማሀበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች | 600 | 192 |
4 | ታዳጊ ክልልና አርብቶ አደር አካባቢ የተየፈጥሮና ማሀበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች | 600 | 186 |
5 | ማሀበራዊ ሳይንስ ዓይነስውራን ወንድ ተማሪዎች | 500 | 160 |
6 | ማሀበራዊ ሳይንስ ዓይነስውራን ሴት ተማሪዎች | 500 | 155 |
7 | በፕሪፓራቶሪ ፕሮግራም የተየፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች | 700 | 238 |
8 | በፕሪፓራቶሪ ፕሮግራም የተየፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች | 700 | 224 |