Skip to content

  • Home
    • Services
  • Document Library
    • Books Grade 1 – 8
    • Grade 9 Text Books
    • Grade 10 Text Books
    • Grade 11 Text Books
    • Grade 12 Text Books
  • Educational Video
    • Grade 9 Educational Videos
    • Grade 10 Educational Videos
    • Grade 11 Educational Videos
    • Grade 12 Educational Videos
  • Notice
  • Contact Us
  • Feedback

የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ይዘቶች ይፋ ሆኑ፡፡

(ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም) ተማሪዎች፣ የተማሪ ቤተሰቦች፣ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ለፈተና ዝግጅት በሚያደርጉበት ወቅት ፈተና የሚሸፍናቸውን የይዘት አካባቢዎች ማወቅ አስፈላጊ መሆኑ ይታመናል። በመሆኑም የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ከፍል ፈተና ዝግጅትና አስተዳደር የሚከተሉትን ያካትታል፡፡

  1. የትምህርት ዓይነቶችን በተመለከተ ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዝክስና ባዮሎጂ እንዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣ ታሪክ፣ ጂኦግራፊና ኢኮኖሚክስ ናቸው።
  2. ፈተናው ከ9ኛ እስከ 12ኛ ከፍል ደረጃዎችን እና በተማሪው መጽሐፍ ላይ ያሉትን ሁሉንም ምዕራፎች ይሸፍናል፡፡
  3. ከ10ኛ – 12ኛ ክፍል ሁሉም የትምህርት ዓይነቶች ፈተና በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት እየተዘጋጀ ያለ ሲሆን የ9ኛ ክፍል ደግሞ የሁሉም የትምህርት ዓይነቶች ፈተናዎች ከቀድሞውና ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርቶች የጋራ ይዘቶችን ብቻ አካቶ እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡
  4. ፈተናው ማንኛውም ተፈታኝ ተማሪ ከተማረው ሥርዓተ ትምህርትና ከተማሪው መጽሐፍ ላይ ብቻ ተመስርቶ የሚዘጋጅ ይሆናል፤
  5. የፈተናው አስተዳደር በበይነ መረብና በወረቀት ጎን ለጎን የሚሰጥ ሲሆን አብዛኛው ተፈታኝ በበይነ መረብ እንዲፈተን እየተሠራ ያለ በመሆኑ ተፈታኞች እራሳቸውን በበይነ መረብ ለመፈተን ሊያዘጋጁ እንደሚገባ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል፡፡

Post navigation

Previous: የኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር ለፌደራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመምህርነት ለተመዘገባችሁ ተወዳዳሪዎች በሙሉ፤
Next: ለ12ኛ ክፍል ተፈታኝ የሆናችሁ ተማሪዎች በሙሉ

Recent Posts

  • The Harare Regional Education Bureau announced that special attention is being paid to all secondary schools in the region to achieve high results in the 2018 national 12th grade examination.
  • Dire Dawa City Administration Education Bureau is working hard to maintain the quality of education;
  • It was stated that schools are working with special attention to achieve better results in the 12th grade national examination.
  • Teachers and school leaders are being encouraged to attend technology-based capacity building training.
  • The inauguration ceremony of the Wolisso Federal Special Boarding School was held at Ambo University.
February 2026
M T W T F S S
 1
2345678
9101112131415
16171819202122
232425262728  
« Jan    

Our Visitor

0 0 9 7 8 3
Views Today : 8
Views Last 7 days : 158
Views Last 30 days : 809
Views This Month : 394
Views This Year : 811
Total views : 17770
Who's Online : 0

Contact Us:

Ministry of Education - Schoolnet ict

Address - Mexico Brewery factory

moe.educational.tv@gmail.com

  • Facebook
  • YouTube
  • Telegram

Related Sites

FDRE Ministry of Education

FDRE Education and Training Authority (ETA)

National Educational Assessment and Examination Agency

Ethernet

Useful Educational Sites

Khanacademy

Learn English for Pre-KG

Africa Complete

Copyright © 2024 Powerd by Schoolnet ICT