ማስታወቂያ
በተዘጋጁ ረቂቅ መመሪያዎች ላይ ግብዓት ለማሰባሰብ የቀረበ ጥሪ
ትምህርት ሚኒስቴር ሥራውን በተገቢው ሁኔታ ለማከናወን ይችል ዘንድ የተለያዩ የአሰራር ሥርዓቶችን የመዘርጋትና መመሪያዎችን የማዘጋጀት ተግባራትን ሲከውን መቆየቱ ይታወቃል። ከዚህ አንጻር፣
- የርቀት ትምህርት ፕሮግራም፣
- የማታ ትምህርት ፕሮግራም፣ እና
- የተፋጠነ ትምህርት ፕሮግራም ማስፈጸሚያ መመሪያዎችን በአዲስ መልክ አዘጋጅቷል።
በመሆኑም የተዘጋጁትን ረቂቅ መመሪያዎች አፅድቆ ሥራ ላይ ለማዋል በረቂቆቹ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በውይይት የማዳበር ሥራ ተሰርቷል። ነገር ግን ተጨማሪ ግብዓት በማሰባሰብ መመሪያዎቹን የበለጠ ማዳበር አስፈላጊ በመሆኑ ፕሮግራሞቹን በመተግበር ላይ ያላችሁ (የርቀት ትምህርት ፕሮግራም ተግባሪ ተቋማት፣ የማታ ትምህርት ፕሮግራም ተግባሪ ተቋማት እና የተፋጠነ ትምህርት ፕሮግራም ተግባሪ ተቋማት) አስተያየት ለመስጠት የተጋበዛችሁ ስለሆኑ መስከረም 14/ 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 በኢፊዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው መድረክ በመገኘት እንድትሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን።
MoE