የትምህርት  ሚኒስተሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አመራሮች ጋር ውይይት አካሄዱ።


ጥቅምት 19/2016 ዓ.ም (ትምህርት ሚኒስቴር)  የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር  36ኛ መደበኛ የምክር ቤት ስብሰባውን በጅግጅጋ ከተማ አካሂዷል።

የትምህርት ሚኒስትሩ በስብሰባው ማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ በመገኘት ከሁሉም ክልሎች ከመጡ የመምህራን ተወካዮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የመምህራን ማህበር የመምህራንን  ክብር ወደ ነበረበት ለመመለስ ጠንክሮ መሥራት ይኖርበታል ብለዋል።

የመምህራንን ክብር ለመመለስ የማስተማር ፍቅርና ችሎታው ያላቸውን መምህራንን ወደ ሙያው ላይ እንዲመጡ ማድረግና ያለ ችግር መኖር የሚያስችላቸው ደመወዝ መክፈል ይገባል ብለዋል።

የሙያ ማህበሩም በበኩሉ የመምህሩን  የትብብር    ጉልበት ተጠቅሞ እንደ ኮኦፕሬቲቭ ባንክ  የመሣሠሉትን በራሱ አባላት በማቋቋም የመምህራን ኑሮ ለማሻሻል መስራት ይኖርበታል ያሉ ሲሆን ትምህርት ሚኒስቴርም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።

አሁን ባለንበት ሁኔታ ሀገራዊ ችግር ውስጥ የገባነው የትምህርት ስርዓታችን በመውደቁ ነው ያሉት ሚኒስትሩ እንደ መምህራን ማህበር ችግሩን በግልፅ ተነጋግሮ ለመፍትሄው በጋራ መስራት ይጠበቃልም ብለዋል።

የሙያ ማህበሩም የሙያውን ክብር ለመመለስ ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት ማድረግና ተጠያቂነት እንዲሰፍን መሥራት እንደሚኖርበት ጠቁመዋል።

ሙሉ ዜናው👇

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0D3kfj6BaB8Sqzh2NFyReJfPtERzutYb7mVpgJNhkzSrVPF8CNwXCJTzGUAAFwfURl&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO።