ጥቅምት 28/2016 ዓ/ም (የትምህርት ሚኒስቴር) በፈረንሳይ፣ ፓሪስ ከተማ ትናንት በተጀመረው 42ኛው የዩኔስኮ አጠቃላይ ኮንፈረንስ ላይ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የትምህርት ሚኒስትርና የብሔራዊ ዩኔስኮ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን እየተሳተፈ ይገኛል::

እ.ኤ.አ. ከኖቬምበር 7 እስከ 22 ቀን 2023 በሚካሄደው ኮንፈረንስ ላይ በአገራችን ውስጥ ባለፉት ሁለት ዓመታት በዩኔስኮ ዘርፎች የተከናወኑ ተግባራት የብሔራዊ ፓሊሲ ንግግር ፣ ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው የአገር መሪዎች ፣ መንግሥት እና ከፍተኛ የትምህርት ሚኒስትሮች የሚሳተፉበት ስብሰባ፣ 13ኛው የወጣቶች መድረክ እንዲሁም እ.ኤ.አ. በ1972 የተደረገው የዓለም ቅርስ ኮንቬንሽን አባላት ጠቅላላ ጉባኤ በኮንፈረንሱ የሚጠበቁ ልዩ ስብሳባዎች ናቸው።

ክቡር ሚኒስትሩ ከኮንፈረንሱ ጎን ለጎን ከተለያዩ አገራት ሚኒስትሮች እና የዩኔስኮ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የሁለትዮሽ ውይይት ያደርጋሉ።

ሙሉ ዜናው 👇

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0FLZLSMcj9ZEaSM6g6ThCJRpFXtrev5k9Auhzh9zUCN1Na2J6gSpediZy7tSmUr6Xl&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO